40 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፌስታል የዋጠው አሳ ነባሪ ህይወት አልፏል

News, News - አረንጓዴ

ምድራችን ባልተመጠነ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ በየግዜው አስጊነቱ እየጨመረ በመጣ ሁኔታ እየተበከለች ትገኛለች። የከባቢ ብክለት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው። መጨረሻው ግን የፍጥረታት ከምድር ላይ መመናመን ከዛ ላቅ ሲልም ከምድረ ገፅ መጥፋት ነው። ፍጥረታት ስንል ታድያ የችግሩ ፈጣሪ የሆነውን የሰው ልጅን ጨምሮ ማለታችን ነው።

በሰው ልጆች እንቅስቃሴ ክፉኛ ከሚጎዱት ፍጥረታት መካከል የባህር እንስሳት ምናልባትም ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ለዚህ ማሳያው ደግሞ በየግዜው ወደ ውሃ አካላት የሚለቀቁ በካይ ቆሻሻዎች በአያሌው መጨመር ነው። የባህር እንስሶች ላይ እየደረሰ ያለው የከፋ ጉዳት እንገነዘብ ዘንድ ከሰሞኑ ከወደ ፊሊፒንስ ያገኘነውን ዜና እናስነብባችሁ።

አንድ አሳ ነባሪ በፊሊፒንሷ ማቢኒ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ መሞቱን የተነገራቸው የባህር ተመራማሪዎች የአሳ ነባሪውን ሬሳ ወደ መመርመርያ ጣቢያቸው በመውሰድ የሞቱን ምክንያት ለማጣራት ጥናታቸውን ይጀምራሉ። በዚህም አሳ ነባሪው በዋጠው የበዛ ፌስታል መጠን ምክንያት ውሀ መጠጣትም ሆነ ተጨማሪ ምግብ መብላት ስላልቻለ ህይወቱ እንዳለፈ ይረዳሉ።

ይህ አስደንጋጭ ክተት ምድራችን በምን አይነት ፍጥነት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እየገባች መሆኗን ማሳያ ነው። በተለይም ሁላችንም በቀን ከቀን ህይወታችን የምንጠቀመው ፌስታል አጠቃቀሙን ማስተካከል ካልተቻለ ለምድራችን ማጥፊያ ዋናው መሳርያ መሆኑን ልናስተውል ይገባል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስትም ከግዜያቶች በፊት የፌስታል አጠቃቀምን የሚደነግግ ህግ እንደሚያወጣ ሲናገር መሰንበቱ ይታወሳል።

ምንጭ: CNN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *