የግራሚ አዋርድ እጩው ኤርትራዊ ራፐር ተገደለ

News, News - Entertainment

ቲኤምዚ ሪፖርት እንዳደረገው በመድረክ ስሙ ኒፕሲ ሀስል በመባል የሚታወቀው ኤርትራዊ ራፐር ኤርምያስ አስገዶም ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ‘ዘ ማራቶን’ በተባለው ሱቁ በር ላይ ቆሞ በነበረበት ግዜ በወረደበት የተኩስ እሩምታ ህይወቱን አጥቷል።

የ33 ዓመቱ ኤርምያስ እ.ኤ.አ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ የቆየ ሲሆን “ቪክትሪ ላፕ” በሚል መጠርያ የመጀመርያ አልበሙን ለአድማጮች ማቅረብ ችሏል። አርቲስቱ እንደ ሪክ ሮስ ፣ ድሬክ ፣ ስኑፕ ዶግ ፣ ፍሬንች ሞንታና እና ቻይልዲሽ ጋምቢኖ ከመሳሰሉ የዘርፉ ስመጥር ባለሙያዎችም ጋር በጥምረት ስራዎችን ሰርቷል።

ኤርምያስ የህይወት አጋሩ ከሆነችው እውቅ ተዋናይት ሎረን ለንደን የ2 ዓመት ወንድ ልጅ ያፈራ ሲሆን ከበፊት ግንኙንቶች የወለዳቸው ሌሎች ልጆችም አሉት።

‘ሮሊን 60’ ከሚባል የወንበዴዎች ቡድን ጋር የነበረውን ግንኙነት ለፎርብስ መፅሄት በሰጠው ቃለ መጠይቅ የገለፀው አርቲስቱ በአሁኑ ሰዓትም በቡድኑ ውስጥ ሆኜ ያጠፋሁን ጥፋት ለመካስ እሰራለሁ ብሎም ነበር። ከዚህ ቡድን ጋር የነበረው ግንኙነት ለሞቱ ምክንያት ይሆናል የሚል ግምት ቢኖርም እስካሁን በግድያው ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው ግን የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *