6ኛው የጉማ ፊልም ሽልማት ሊካሄድ ነው

News, News - Entertainment

በኢትዮ ፊልም አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የጉማ ፊልም ሽልማት የፊታችን መጋቢት 16 በብሄራዊ ቴአትር ቤት እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።

ዘንድሮ ለ6ኛ ግዜ የሚካሄደው ይህ የፊልም ሽልማት በ18 ዘርፎች የተመረጡ የሽልማቱን እጩዎች ዛሬ ይፋ ያደረገ ሲሆን ታላቁን ኢትዮጵያዊ የፊልም ጠቢብ ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማን ደግሞ የህይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጎ መምረጡን አሳውቋል።

በ5ኛው የጉማ ሽልማት ላይ ዘሪቱ ከበደ በምርጥ ሴት ተዋናይት ዘርፍ ፣ ካሳሁን ፍስሀ እና መሰረት መብራቴ በምርጥ አለባበስ ሲሸለሙ እውቁ የማስታወቂያ ሰው ጋሽ ውብሸት ወርቅአለማሁ ደግሞ የህይወት ዘመን ተሸላሚ የሚለውን ማዕረግ አግኝተዋል።

ይህ ዘንድሮ ለ6ኛ ግዜ የሚደረገው ሽልማት በፊምል ባለሙያው ዮናስ ብርነመዋ ሀሳብ አመንጪነት መጀመሩ የሚታወስ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *