ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በቻይና የሞት ፍርድ ስጋት ተጋርጦባታል

News

ናዝራዊት አበራ የ27 ዓመት ወጣት ስትሆን የኢንጅነሪንግ የት/ት ዘርፍም ምሩቅ ናት። ታድያ ይቺ ወጣት ሰሞኑን በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ተጠርጥራ በቻይና ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።
አብሮ አደግ ጓደኛዋ አድርሺልኝ ያለቻትን በሻምፖ እቃ ውስጥ የተሞላ ኮኬይን ይዛ በመገኘቷ ነበር በቁጥጥር ስር የዋለችው። ጓደኛዋ ለተወሰነ ግዜ በህግ ቁጥጥር ስር የቆየች ቢሆንም አሁን ግን አድራሻዋን በጭራሽ ማግኘት አልተቻለም።
በቤጂንግ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአሁኑ ሰዓት የናዝራዊትን የፍ/ቤት እና ተያያዥ ወጪዎች እየሸፈነ ቢገኝም ቤተሰቦችዋ እና ጓደኞቿ ግን ናዝራዊት ከታሰረችበት ጃንዋሪ 2019 ጀምሮ እሷን ማግኘትም ሆነ ስለሁኔታዋ ማወቅ አልቻልንም ባይ ናቸው።
በቻይና ህግ መሰረት አደንዛዥ ዕፅ ይዞ መገኘት የሞት ፍርድ ያስፈርዳል። ይኸው ናዝራዊትም የዚህ ቅጣት ፍርደኛ ልትሆን ትችላለች የሚል ስጋት ቤተሰብዋን እየናጠው ይገኛል።

ምንጭ: ዴይሊ ሜይል