ኢቫንካ ትራምፕ በኢትዮጵያ ጉብኝት ልታደርግ ነው

News

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ እና የዋይት ሀውስ አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ በኢትዮጵያ ጉብኝት ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ኢቫንካ ትራምፕ በአውሮፓውያኑ በያዝነው ወር ላይ በአፍሪካ የአራት ቀናት ጉብኝት እንደምታደርግ ዋይት ሀውስ በትናንትናው እለት አስታውቋል።

ኢቫንካ በአፍሪካ ጉብኝቷም ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመጣ ነው የተመለከተው።

የዋይት ሀውስ አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ በጉብኝቷ ወቅትም ከፖለቲካ አመራሮች፣ ሥራ አስፈፃሚዎች እና ሴት ሥራ ፈጠራ ባለቤቶች ጋር ተገናኝታ እንደምትወያይ ይጠበቃል።

ኢቫንካ ትራምፕ ከኢትዮጵያ ጉብኝቷ በተጨማሪም ወደ አይቮሪኮስት በማቅናት ጉብኝት የምታደረግ መሆኑንም ዋይት ሀውስ አስታውቋል።

በአይቮሪኮስት ቆይታዋም በሴቶችን ኢኮኖሚ ማጠንከር ዙሪያ በሚዘጋጅ ጉባሌ ላይ እንደምትሳተፍም ነው የተነገረው።

ኢቫንካ ትራምፕ ጋርም የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) ሀላፊ ማርክ ግሪንን ጨምሮ የዓለም ባንክ እና የግል ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን የስራ ሀላፊዎች ጉብኝት እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ምንጭ፦ www.bloomberg.com ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *