ተወዳጁ ፊልም ዳግም ወደ ሲኒማ ቤት ሊመለስ ነው

News, News - Entertainment

እ.ኤ.አ በ1992 ዓ.ም. ነበር የመጀመርያው አላዲን የተሰኘው ፊልም ለተመልካቾች የደረሰው። ይሄው አሁን ደግሞ ፊልሙ እንደገና በአክሽን የፊልም ዘውግ ተሰርቶ ለተመልካች ሊደርስ መሆኑን ከወደ ዲስኒ የተሰማው ዜና ይዘግባል።
በጋይ ሪቺ ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም ዊል ስሚዝ ፣ ነቪድ ኔጋባን ፣ ፍራንክ ዎከር ፣ ማርዌን ኬንዛሪን እና ጃዝመን ማናን እንደሚያካትት ለማወቅ ተችሏል።
በፊልሙ ውስጥም የግራሚ አሸናፊ የሆነው “ኤ ሆል ኒው ወርልድ” የተሰኘው ሙዚቃ ማጀቢያ ሆኖ ገብቷል። ሙዚቃው በምርጥ የማጀቢያ ሙዚቃ ዘርፍ የኦስካር ሽልማትንም ማሸነፍ የቻለ ነው።
አዲሱ አላዲን ፊልም ከሜይ 24 ጀምሮ ለእይታ ይበቃል።

ምንጭ: ሲኤንኤን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *