ሩዋንዳ – የእውነት እኩልነት ወይንስ የታይታ?

News, News-ሔዋን

ሩዋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሴቶች ወደ ፖለቲካ ስልጣን በማምጣት በአለም ከፍተኛ አድናቆትን አግኝታለች። የፓርላማውን 60 ፐርሰንት ፣ የካቢኔውን እና የጠቅላይ ፍ/ቤት የዳኝነት ቦታ ደግሞ በ50 ፐርሰንት ሴቶች ይዘውት እናገኛለን። ጥያቄው ግን ይህ ቁጥር ከአሀዝ በዘለለ ለሀገሪቱ ምን ፈይዷል የሚለው ነው።
አለም አቀፍ ኢኮኖሚክ ፎረም ባወጣው የፆታ ተዋፅኦ ሰንጠረዥ ላይ ሩዋንዳ ከአለም የ6ኛነት ደረጃን ይዛለች። በዚሁ ሰንጠረዥ ላይ ኢትዮጵያ የ117ኛነት ደረጃን ይዛ ትገኛለች። ምንም እንኳን ሴቶች በዚህን ያህል ቁጥር ወደ ስልጣን መምጣት ቢችሉም በሀገሪቷ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሰሚነት ግን እምብዛም ነው። ለምሳሌ ሴቶችን የተመለከቱ ህጎችን በማፀደቅ በኩል እስካሁን ምንም አይነት ለውጥ እንደሌለ ይነገራል። “ሌላው ቀርቶ የወሊድ ፈቃድ እንኳን ከ 12 ሳምንታት ሊዘል አልቻለም” ስትል አንዲት ነዋሪነቷን በኪጋሊ ያደረገች ጦማሪት ምሬቷም ለ ዲደብልዮ ተናግራለች።
ስለዚህም ትላለች ይችው ጦማሪ “የነሱ ወደ ስልጣን መምጣት ለታይታ እንጂ በርግጥም የውሳኔ ሰጪነት እና የተሰሚነትን እኩልነት ማረጋገጥ የቻለ አይደለም።”
“ጓደኛህ ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ” ነው እና ብሂሉ ሀገራችንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየወሰደችው ያለው ሴቶችን በፖለቲካ ሹመት የማምበሽበሽ እርምጃ እንደ ሩዋንዳ ሁሉ የታይታ ሆኖ ይቀር ይሆን ብለን እንድንጠይቅ ግድ ይለናል።

ምንጭ: ዲደብልዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *